Fana: At a Speed of Life!

በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ ለሚከናወን የመስኖ መሰረተ-ልማት አውታር ግንባታ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ሲዳማ ክልሎች የሚተገበሩ የመስኖ መሰረተ-ልማት አውታር ግንባታዎችን ለማስጀመር ከአራት ሀገር በቀል ተቋራጭ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ተፈረመ፡፡

ስምምነቱ የተፈረመው በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር እና በአራት ሀገር በቀል ተቋረጭ ድርጅቶች መካከል ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ የግብርና ምርታማነት በማሳደግና ለግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ጥሬ እቃ በማቅረብ ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአፍሪካ ልማት ባንክ ድጋፍ የሚሰራው ይህ ፕሮጀክት 10 ሺህ ሄክታር ማልማት የሚያስችል መሆኑንም ነው የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዴዔታ ብርሃኑ ሌንጂሶ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የገለጹት፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.