Fana: At a Speed of Life!

የከባድና ተሳቢ መኪና አምራቾችን የገበያ ትስስር ችግር ለመፍታት የሚያስችል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የከባድና ተሳቢ መኪና አምራች ኢንዱስትሪዎችን የገበያ ትስስር ችግር ለመፍታት የሚያስችል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

መድረኩ የትራክና ተሳቢ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በማስተዋወቅ መኪኖቹን ከሚገዙ ደንበኞች ጋር የንግድ ትስስር በመፍጠር ያሉባቸውን የገበያ ችግር ለመፍታት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

በውይይቱ አምራቾች ምርታቸውን በጥራትና በጊዜ ተደራሽ ከማድረግ አንፃር የገጠሟቸውን ችግሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት የአምራቾችን አቅም መለየትና ቀጣይነት ያለው የገበያ ትስስር የሚፈጠርበት መድረክ ይሆናል ተብሏል፡፡

መድረኩን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እንዳዘጋጀው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ እና የትራንስፓርትና ሎጀስቲክ ሚኒስትር ዴኤታ ዳንጌ ቦሩ እንዲሁም የከባድ፣ ተሳቢ መኪና አምራቾች ገዥዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.