የሁቤይ ግዛት ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ተሰማርተው የስራ እድል በመፍጠር ሚና እየተጫወቱ ነው – አምባሳደር ተፈራ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁቤይ ግዛት ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ተሰማርተው የስራ እድል በመፍጠር ሚና እየተጫወቱ ነው ሲሉ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ተናገሩ፡፡
አምባሳደሩ በግዛቷ “ጎ ግለባል” በሚል በተዘጋጀው የትብብር ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ እና የሁቤይ ግዛት ጠንካራ የኢኮኖሚ ትስስር እንዳላቸው ገልፀዋል።
ጉባኤው በኢትዮጵያ እና በግዛቷ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማሳደግ የሚያስችል መድረክ መሆኑንም ተናግረዋል።
የሁቤይ ግዛት ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው እንደሚገኙ የገለፁት አምባሳደሩ÷ ኩባንያዎች ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር እና ገቢ በማስገኘት ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻዎቹን በተለያዩ ዓለማት እያሰፋ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ አየር መንገዱ በኢትዮጵያ እና በሁቤይ ግዛት ያለውን የኢኮኖሚ ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከቻይና እና ከሁቤይ ግዛት ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት ለማሳደግ እና ለማሻሻል ሁሌም ቁርጠኛ ነች ማለታቸውን ከቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!