የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም ሂደት ካናዳ በምትደግፍበት ሁኔታ ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም ሂደት ካናዳ መደገፍ በምትችልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በካናዳ የዓለምአቀፍ ጉዳዮች የሴቶች የሠላም እና ደኅንነት አምባሳደር ከሆኑት ጃኮሊን ኦ ኔል ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡
ውይይታቸው ፍሬያማ እንደነበረ እና ከኮሚሽኑ ሥራ ጋር በተያያዘ ካናዳ ድጋፍ በምታደርግበት አግባብ ላይ መምከራቸውን ኮሚሽነሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡