Fana: At a Speed of Life!

የአልትራሳንውንድ ሕክምና መሳሪያ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ጋርመንት የሚገኘው ሁዋጂያን ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የአልትራሳንውንድ ሕክምና መሳሪያ መገጣጠሚያ ፋብሪካ በዛሬ ዕለት ሥራ ጀምሯል።

ኤልስሜድ ሶሊሽንስና ሲመንስ የተሰኙ ኩባንያዎች በጋራ ኢንቨስት ያደረጉበት ፋብሪካው÷ የተለያዩ ዓይነት ህመሞችን መመርመር የሚያስችሉ መሳሪያዎች እንደሚገጣጠሙበት ተገልጿል፡፡

የፋብሪካው ወደ ሥራ መግባት ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ በላቀ ቴክኖሎጂ ሕክምናን ተደራሽ ለማድረግ ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ፍሬሕይወት አበበ ተናግረዋል፡፡

የኤልስሜድ ሶሉሽን ኩባንያ ፕሬዚዳንት ሮኔን ባሁር በበኩላቸው÷ ከረጅም ዓመታት ዝግጅት በኋላ የፋብሪካው እውን መሆን አስደስቶናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በፋብሪካው የሚመረቱ መሳሪያዎች በኢትዮጵያ የተሠራ /ሜድ ኢን ኢትዮጵያ/ መለያ ብራንድ የሚጻፍባቸው በመሆኑ ለኢትዮጵያ ኩራት ነው ያሉት ደግሞ የኤልስሜድ የኢትዮጵያ ተወካይ ዳዊት ኃይሉ ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.