Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ታዬ ከቱኒዚያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከቱኒዚያ አቻቸው ናቢል አሚር ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ሚኒስትርቹ እየተካሄደ ካለው 44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን ነው የተወያዩት፡፡

በውይይታቸውም ሀገራቱ በሁሉም መድረኮች በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮ-ቱኒዚያ የጋራ የሚኒስትሮች ስብሰባ በተቻለ ፍጥነት እንዲደረግ መግባባት ላይ መደረሱም ተጠቁሟል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በመርሕ ላይ ተመሥርቶ የአፍሪካን አጀንዳ በጋራ ማራመድ እንዲቻል መወያየታቸውም ተገልጿል፡፡

#Ethiopia #Tunisia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.