Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚካሄደውን የሕዝባዊ የውይይት መድረክ ለመምራት ከፍተኛ አመራሮች አርባምንጭ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነገ የሚካሄደውን ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ለመምራት ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል፡፡

በነገው ዕለት “ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና”በሚል መሪ ሐሳብ በ20 ከተሞች ሕዝባዊ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡

በአርባምንጭ ከተማ የሚካሄደውን መድረክ ለመምራትም የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ እና የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሳዳት ነሻ አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል፡፡

የሥራ ኃላፊዎቹ አርባምንጭ ሲገቡም የጋሞ ዞን አመራሮች እና የጋሞ አባቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በተመሳሳይ በክልሉ የሚካሄደውን ህዝባዊ ውይይት ለመምራት ዲላ ከተማ የገቡት በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ ይገዙ ናቸው።

የሥራ ሃላፊዎቹ ዲላ ከተማ ሲገቡ የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

እንዲሁም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና የዲሞክራሲ ግንባታ ተቋም ፖለቲካና ርዕዮተ-ዓለም ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) የሕዝባዊ ውይይት መድረክ ለመምራት ወላይታ ሶዶ ከተማ የገቡ ሲሆን፤ የክልል እና የዞን አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.