የሎጎ ሐይቅን ለማልማት የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለተኛው የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት የሚለማው የሎጎ ሐይቅ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡
የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደን ጨምሮ የፌደራልና የክልል የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች የፕሮጀክቱን የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተመልክተዋል።
በዚሁ ወቅት አቶ አረጋ እንዳሉት ÷ በክልሉ ያሉትን የጎብኝ መዳረሻ ስፍራዎች ለማልማት መንግሥት በልዩ ትኩረት እየሠራ ነው።
ፕሮጀክቱም 14 ሄክታር እንደሚሸፍን ጠቅሰው÷ ይህም ለክልሉ የቱሪዝም ዘርፍ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡
ሎጎ ሐይቅ ከደሴ ከተማ በስተ ሰሜን አቅጣጫ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን÷ በውስጡም ቀረሶ፣ ዱቤና አምባዛ የተሰኙ ሦስት ዓይነት የዓሣ ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡
በአማካይ 23 ሜትር ጥልቅት እና 35 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ሐይቁ÷ ከባህር ወለል በላይ 1 ሺህ 950 ሜትር ከፍታ ላይ ያረፈ ነው፡፡
በኢሳያስ ገላው