Fana: At a Speed of Life!

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 679 ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ 594 እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ 85 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው።

የዩቨርሲቲው ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ሰብስቤ ደምሰው (ፕ/ር) በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በሰለጠናችሁበት መስክ ስራ በመፍጠርና ችግር ለመፍታት አደራ የምትቀበሉበት ዕለት ነው ብለዋል።

በተማራችሁበት ዘርፍ ለሀገርና ለትውልድ ፋይዳ ያለው ስራ በመስራት አደራችሁን ልትወጡ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

ተመራቂዎች የሀገር ተስፋ እና የለውጥ ዓርማዎች መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ሙክታር መሐመድ (ፕ/ር) ናቸው፡፡

ታማኝነት፣ ተጠያቂነትና ትጋት መለያቸው ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበው፤ ወደ ስራ ዓለም ሲገቡ የማህበረሰቡን እሴት በማክበር የአገልጋይነት ባህሪ በመላበስ ሀገርን የሚያሻግር ትውልድ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ከ7 ሺህ 200 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።

በነጌሶ ከዲር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.