በአርሲ ዞን ሌሙና ብልብሎ ወረዳ 3 ሺህ 700 ሕገ ወጥ ጥይት ተያዘ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሌሙና ብልብሎ ወረዳ 3 ሺህ 700 ሕገ ወጥ ጥይት መያዙን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ሕገ-ወጥ ጥይቱ ከሻሸመኔ ከተማ ወደ መጪቱ ከተማ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ነው የተያዘው፡፡
ከጥይቱ በተጨማሪ የተለያዩ ሕገ-ወጥ እቃዎች እና ሶስት ተጠርጣሪዎች መያዛቸውንም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡