Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው “ለነገዋ” የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከልን መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው “ለነገዋ” የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከልን መርቀው ከፍተዋል፡፡

“ለነገዋ” የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶችን ለሚጋፈጡ ሴቶች መደገፊያ እንዲሆን መቋቋሙ ተገልጿል፡፡

ማዕከሉ ከሥነ-ልቡና ድጋፍ እና የጤና ክብካቤ ጀምሮ ሙያዊ ስልጠናዎችን ይሰጣልም ተብሏል፡፡

በተጨማሪም አዳዲስ የስራ ስምሪት መንገዶችን የሚፈጥር እና ሴቶች በማኅበረስቡ ውስጥ ለሚገባቸው ተገቢ ስፍራ ብቁ የሚያደርግ እንደሚሆንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.