Fana: At a Speed of Life!

በግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በብራዚል የሥራ ጉብኝት እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በብራዚል የሥራ ጉብኝት እያደረገ ነው።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ጉብኝት በብራዚል በግብርናው ዘርፍ የተሰሩ ሥራዎችን ልምድ ለመቅሰም ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በብራዚል በምርትና ምርታማነት ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮት የተፈቱባቸው ዘዴዎችን እና የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በምርት ዕድገት ላይ አዎንታዊ እመርታ ማስመዝብ የተቻለበት ሒደትንም ልዑኩ ተመልክቷል፡፡

የብራዚል መንግስት የዜጎችን የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ከመቻል አልፎ የግብርና ውጤቶችን ወደ ውጭ በመላክ በኢኮኖሚያቸው ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት እንደቻሉም መነገሩን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

ብራዚል እና ኢትዮጵያ ወቅታዊ እና ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ሲሆኑ÷ ሁለቱም ሀገራት የቡድን 77፣ የብሪክስ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባላት ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.