Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ብሄራዊ አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (አ6ፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ብሄራዊ አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ የመክፈቻና የግንዛቤ መስጫ መድረክ መካሄዱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ “ዘላቂ የክትመት ምጣኔ ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን – አጀንዳ 2063” በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በመጭው መስከረም በአዲስ አበባ ይካሄዳል ብለዋል።

በዛሬው ዕለትም የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ብሄራዊ አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ የመክፈቻና የግንዛቤ መስጫ መድረክ መካሄዱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ታሪካዊት፣ የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ አፍሪካ ህብረት መስራች ሀገር መሆኗን አስታውሰው፤ ይህንን ከ1 ሺህ 500 በላይ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙበት የሚጠበቀውን የአፍሪካ ወንድማማቾች መመካከሪያ መድረክ ለማዘጋጀት የተሰጣትን አፍሪካዊ ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት ዝግጁ መሆኗን በመድረኩ ተግባብተናል ሲሉ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.