Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረት ስራ ኤጀንሲዎች ባዛርና ዓውደ ርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ክልል አቀፍ የህብረት ስራ ኤጀንሲዎች ባዛርና ዓውደ ርዕይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ተከፈተ።

የህብረት ስራ ማህበራት ለሁለንትናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው ባዛርና ዓውደ ርዕዩ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም አምራች ህብረት ስራ ማህበራት እንደሚሳተፉበት ተመላክቷል፡፡

በዚህም የግብርና ምርቶች፣ የኢንዱስትሪ ምርቶችና ሌሎችም የፈጠራ ስራዎች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

ባዛሩን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከፍተውታል፡፡

ኃላፊዎቹ በአሁኑ ሰዓት ምርቶቹን እየጎበኙ ሲሆን፤ ባዛርና ዓውደ ርዕዩ ለአምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ተጠቁሟል።

በጥላሁን ይልማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.