አቶ ሙስጠፌ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ አሳሰቡ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጂግጂጋ ከተማ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ግንባታ እያከናወኑ ያሉ ተቋራጮች ሥራቸውን በማፋጠን በተቀመጠላቸው ጥራትና ጊዜ እንዲያጠናቅቁ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ አሳሰቡ፡፡
ርዕሰ መሥተዳድሩ በጂግጂጋ ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኙትን÷ የክልሉ ፖሊስ አጠቃላይ ሆስፒታልን፣ የመንገድና ድልድይ ሥራን ጨምሮ የእናቶችና ሕጻናት ሆስፒታል የግንባታ ሒደትን ተመልክተዋል።
በዚሁ ወቅትም የፕሮጀክቶቹን ግንባታ የሚያከናውኑ ተቋራጮች ግንባታቸውን በማፋጠን እና ፕሮጀክቶቹን በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ አጠናቅቀው እንዲያስረክቡ ማሳሰባቸውን የክልሉ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡