የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቀብሪደሃር የበረራ አገልግሎት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሶማሊ ክልል ቀብሪደሃር ከተማ የበረራ አገልግሎት ጀምሯል።
የቀብሪደሀር አየር ማረፊያ አካባቢ በተከታታይ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በአየር ማርፊያው በደረሰው ጉዳት የበረራ አገልግሎቱ ተቋርጦ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
ይሁን እንጂ የአየር ማረፊያው ያጋጠመው ጉዳት በፍጥነት ተጠግኖ የበረራ አገልግሎቱን በዛሬው እለት በድጋሜ መጀመሩ ተገልጿል፡፡
አየር መንገዱ ወደ አገልግሎት መመለሱ የቀብሪዳሀር እና አባቢውን የትራንስፖርት ችግር በከፍተኛ ደረጃ ያቃልላል መባሉን ከሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡