Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የዞኖች የ9 ወራት ሥራ አፈፃፀም ግምገማ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል 11 ዞኖች የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ የዘጠኝ ወራት ሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ መድረክ በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፅህፈት ቤት መካሄድ ጀመረ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሀመድ እንደገለጹት፤ በመድረኩ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በፀጥታ፣ በመሰረተ ልማትና በሌማት ትሩፋት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተሰሩ ስራዎች ይገመገማሉ።

በዚህም በክልሉ 11 ዞኖች፣ 95 ወረዳዎችና 2 ሺህ 500 ቀበሌዎች ላይ የተከናወኑ ሥራዎች የሚገመገሙ መሆኑን መጠቆማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል።

የክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ መካሄዱ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.