የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ‘ጽዱ ኢትዮጵያ’ ንቅናቄን ተቀላቀሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የሆነውን ‘ጽዱ ኢትዮጵያ’ ንቅናቄን ተቀላቀሉ።
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አመራር፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ያለውን ንቅናቄ በመቀላቀል ድጋፍ አድርገዋል።
የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ለንቅናቄው ዓላማ መሳካት ሁሉም በንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248 አስተዋጽኦ በማድረግ እንዲቀላቀል ጥሪ ማቅረባቸውን የዩኒቨርሲቲው መረጃ አመላክቷል።
#ጽዱ_ኢትዮጵያ