Fana: At a Speed of Life!

ዜጎች ለ #ጽዱኢትዮጵያ በዲጂታል ቴሌቶን የሚያደርጉት ድጋፍ ቀጥሏል – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዜጎች ለ #ጽዱኢትዮጵያ በዲጂታል ቴሌቶን የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

#ጽዱኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶን ከተጠናቀቀበት ግንቦት 4 ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ ንቅናቄው ሳይቆም በመቀጠሉ የተገኘ ተረፈ ‘የ50 ሚሊየን ብር በአንድ ጀምበር’ ዲጂታል ቴሌቶን የተጨማሪ አንድ ቀን ገቢ 61,753,172.47 ብር መሆኑ ተገልጿል::

#ጽዱኢትዮጵያ በግንቦት 4 እና 5 ቀን የተገኘው ገቢ ድምርም 216,253,172 ብር መድረሱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.