Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የሜዳይ፣ ኒሻንና ሽልማት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 26ኛ መደበኛ ስብሰባው የሜዳይ፣ ኒሻንና ሽልማት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

የውሳኔ ሃሳቡን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) የረቂቅ አዋጁን አስፈላጊነት አስመልክተው እንደገለጹት ፥ በሀገራችን፣ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዘርፎች ለሀገርና ለህዝብ የሚጠቅም የላቀ ተግባር የፈጸሙ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችንና አካላትን እውቅና በመስጠት ትውልዱን ማነሳሳት አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡

ረቂቅ አዋጁ በህገ-መንግስቱ መሰረት ማስፈጸሚያ አዋጅ ሳይወጣላቸው እየተሰጡ ያሉ የተለያዩ የሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት ሂደቶችን በማስቀረት ወጥ የሆነ ህጋዊ አሰራር እንዲኖር ማድረግ በማስፈለጉ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ምክር ቤቱም የተሰጠውን ማብራሪያ ተቀብሎ ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 1325/2016 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.