Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኢትዮ-ቴሌኮምን የተሞክሮ ማዕከል ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባውን የኢትዮ-ቴሌኮም የተሞክሮ ማዕከል ጎበኙ።

የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በአቶ ሽመልስ አብዲሳ ለተመራው ልዑክ ስለ ማዕከሉ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማዕከሉም ኢትዮ ቴሌኮም ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ልህቀት የሚያሳዩ ተሞክሮዎች እንዳሉ ለጎብኘዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ከ2ጂ እስከ 5ጂ ኔትዎርክን በመተግበር ከተንቀሳቃሽ እስከ መደበኛ የስልክ ትስስር ከመፍጠር ባለፈ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ሒደት ጉልህ ሚና እየተወጣ ነው ተብሏል።

በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥም እንደ ቴሌ ብር ያሉ መተግበሪያዎችን ወደ ስራ በማስገባት፣ በትሪሊየን የሚቆጠር ግብይት እንዲከናወን ማስቻሉ ነው የተጠቆመው።

በስማርት የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ እና ሌሎች መስኮች እያደረገ ያለው የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ለጎብኝዎቹ ገለጻ መደረጉንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.