Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የመጀመሪያው የሣይንስና የፈጠራ ሥራዎች ዐውደ-ርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመጀመሪያ የሆነው የሣይንስና የፈጠራ ሥራዎች ዐውደ-ርዕይ ተከፈተ፡፡

በታርጫ ከተማ የተከፈተው የመምህራንና የተማሪዎች የሣይንስና የፈጠራ ሥራዎች ዐውደ-ርዕይ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የክልሉ የትምህርት ቢሮ እና ክኅሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ በጋራ ባዘጋጁት ዐውደ-ርዕይ ላይ÷ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች በተማሪዎች የተዘጋጁ የተለያዩ የሣይንስና የፈጠራ ሥራዎች ውጤት ለዕይታ መቅረቡ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.