Fana: At a Speed of Life!

ታማሚ አሳፍሮ ወደ ሆስፒታል ሲጓዝ የነበረ አምቡላንስ ተገልብጦ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዳሰነች ወረዳ ታማሚ አሳፍሮ ለተሻለ ሕክምና ወደ ጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሲጓዝ የነበረ አምቡላንስ ተገልብጦ የሦስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው፡፡

አደጋው የደረሰው በደቡብ ኦሞ ዞን በና ፀማይ ወረዳ አርጎ ቀበሌ አርጎ ቁልቁለት አካባቢ መሆኑን የዳሰነች ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችም በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታ የሕክምና ዕርዳታ እያገኙ ሲሆን÷ የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.