Fana: At a Speed of Life!

የ2017 የፌዴራል መንግሥት በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሂዷል፡፡

ምክር ቤቱ በስብሰባው የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን ተወያይቶ አጽድቋል፡፡

በዚህም የፌዴራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸድቋል፡፡

በጀቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እድገትን ለማፋጠን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን÷ የሚጸድቀውን በጀት በሕግ እና ሥርዓት የመጠቀም ሃላፊነት እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.