አቶ ኡሞድ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ርዕሠ መሥተዳድር ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር አካል የሆነ ችግኝ ተከላ አከናውነዋል፡፡
ርዕሰ መሥተዳድሩ የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ ክልል አቀፍ መርሐ-ግብር ትናንት በጋምቤላ ወረዳ ማስጀመራቸው ይታወሳል።
በዛሬው ዕለትም የመርሐ-ግብሩ አካል የሆነ ችግኝ ተከላ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት መከናወኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
በዚሁ ዕለት አቶ ኡሞድ ባደረጉት ንግግር፤ ዩኒቨርሲቲው በክልሉ ያለውን እምቅ ሀብት በመጠቀም ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን ከማከናወን ጎን ለጎን ለአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ትኩረት እንዲሰጥ አመላክተዋል፡፡
የክልሉ መንግሥትም ዩኒቨርሲቲው ለሚያከናውናቸው ተግባራት ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡