በኦሮሚያ ክልል በ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር ላይ ሩዝ ለማልማት እየተሠራ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሔክታር መሬት ላይ ሩዝ ለማልማት እየተሠራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ገመቹ ገለጹ፡፡
ከዚህም 60 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
ኃላፊው በጅማ ዞን ዴዶ ወረዳ የሩዝ ሰብል ልማት ዘር ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ በ2016 የምርት ዘመን በሩዝ ምርት ከተሸፈነ 1 ሚሊየን ሔክታር 32 ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን አስታውሰዋል፡፡
አርሶ አደሩ የሩዝ ሰብልን የማልማት ልማዱን እያሳደገ መምጣቱን ገልጸው፤ ምርታማነትን በመጨመር የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
በወርቃፈራሁ ያለው