Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ የኮሪደር ልማት ሥራ አፈፃፀም ክትትልና ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አካላትን አመሰገኑ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ የኮሪደር ልማት ሥራ አፈፃፀም ክትትል እና ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አካላትን አመስግነዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷የኮሪደር ልማት ሥራ የእያንዳንዱ ቀን እና ምሽት ሥራ እየተገመገመ የሚከናወን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ልማቱ ለመረጠን እና ቃል ለገባንለት የመዲናዋ ነዋሪ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ትስስር ማጠናከር የሚያስችሉ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ከዘመናዊነት ጋር የተቃኘ አሰራርን በመዘርጋት እና በማሳለጥ ለከተማዋ የኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ሚና እንድንወጣ ያስቻለን ነው ብለዋል፡፡

በሒደቱም በምታደርጉት ተሳትፎ በአዲስ አበባ ፈጣን ለውጥ ውስጥ ታሪካዊ አሻራችሁን እያሳረፋችሁ መሆናችሁን ተረድታችሁ ስራውን በፍጥነት ብቻ ሳይሆን በጥራት እንድትሰሩ አበረታታችኋለሁ ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በታሪክ ሒደት የከተማዋን የሥራ ባህል በቀየርንበት ቀንና ሌሊት በሰራችሁበት ጎን ለሥራ ጥራት የምትሰጡት ትኩረት እንዲሁ ባህል ሆኖ መቀጠል እንዲችል መስራት አለብን ነው ያሉት፡፡

ከንቲባ አዳነች በቦሌ ሳይት በየምሽቱ በሥራ ላይ ለሚገኙ ሰራተኞች የእራት ግብዣ እያደረጉ ላሉ የአካባቢው ነዋሪዎችን አመስግነዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.