Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በግሪክ የክብር ቆንስል ጽሕፈት ቤት ከፈተች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በግሪክ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ጽሕፈት ቤትን መርቀው ሥራ አስጀመሩ፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ በዚሁ ወቅት በግሪክ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ሆነው ለተሾሙት ጂዮርጂዮስ ቢካስ የሹመት ደብዳቤያቸውን አስረክበዋል።

ጂዮርጂዮስ ቢካስ በግሪክ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንዲሠሩም ሚኒስትር ዴዔታው አሳስበዋል፡፡

በተለይም በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ያለውን ግንኙነት በይበልጥ ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱም ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.