Fana: At a Speed of Life!

በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት በዘላቂነት ለመፍታት ተስማምተናል – የክልሎቹ ርዕሳነ መስተዳድሮች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት በዘላቂነት ለመፍታት ከስምምነት መደረሱን የክልሎቹ ርዕሳነ መስተዳድሮች ገለጹ።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት በዘላቂነት ለመፍታት መስማማታቸውን በተመለከተ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም÷በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በዘላቂነት ለመፍታት የክልሎቹና የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ውይይት መደረጉን ተናግረዋል።

በቀጣይም ለግጭቶች ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮችን በመለየት የጋራ መፍትሄ ለመስጠት ስምምነት ላይ ተደርሷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.