Fana: At a Speed of Life!

በቢሾፍቱ ከተማ ከ4 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የተገነቡ 175 ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ ከተማ ከ4 ቢሊየን ብር በሚል ወጪ የተገነቡ ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ 175 ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡

ፕሮጀክቶቹን የመረቁት በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ እና የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ናቸው፡፡

ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከልም ባህላዊ ፍርድ ቤት፣ ጂ+3 የገበያ ማዕከላት ሕንጻዎች፣ የአስፓልት መንገድ፣ ትምህርት ቤት፣ የቢሾፍቱ ከተማ አሥተዳደር ፍርድ ቤት ጽሕፈት ቤት ሕንጻና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.