Fana: At a Speed of Life!

በማድሪድ ብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍት የኢትዮጵያ ቤተ -መጻሕፍት ክፍል ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ማድሪድ ብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍት የኢትዮጵያ ቤተ-መጻሕፍት ክፍል መከፈቱን የአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ዋና ዳይሬክተር  ውብአየሁ ማሞ (ኢ/ር) አስታወቁ፡፡

በሀገሪቱ ብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍት ቅጥር ግቢ የተደራጀው  የኢትዮጵያ ቤተ-መጻሕፍት ክፍል የኢትዮጵያን ታሪክ ባህልና ቋንቋ ለዓለም ለማስተዋወቅ እንዲረዳ መደራጀቱንም ነው የገለጹት፡፡

መጻሕፍቱን በስፔን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሚገባ እንዲጠቀሙባቸው አመች በሆነ የዲጂታል መተግበሪያዎች ሳይቀር መገኘት እንደሚችሉም አስታውቀዋል፡፡

በፈረንጆቹ 1711 የተመሰረተው ታሪካዊው የስፔን ብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍት ከ26 ሚሊየን በላይ የመጻሕፍትን በመያዝ በዓለም ከሚገኙ ስመ ጥር ቤተ -መጻሕፍት ተርታ የሚሰለፍ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያና ስፔን ያላቸውን መልካም ግንኙነት መሰረት በማድረግ በሀገሪቱ ብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍት የተደራጀው የኢትዮጵያ ቤተ-መጻሕፍት ክፍል የሁለቱን ሀገራት የቆየ ወዳጅነት ይበልጥ ያጠናክረዋል ብለዋል፡፡

የአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የአውሮፓ ሕብረት እና ትብብር ተጠሪ ጉሌርሞ ኢስክቫኖ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያውያን የስፓኒሽ ቋንንቋ በነፃ እንዲማሩ መግባባት ላይ ተደርሷል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.