Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ድህነትን ለመቀነስ የሚከናወኑ ተግባራትን የሚደግፍ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ድህነትን ለመቀነስ የሚከናወኑ ተግባራትን የሚደግፍ “ዲፕ ቻሌንጅ ፈንድ” የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ተደርጓል፡፡

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ በኢትዮጵያ በድህነት ቅነሳ ላይ የሚሰሩ የግብርና፣ የፕላንና ልማት፣ የፋይናንስ እና ሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የዓለም ባንክ፣ የዲፕ ቻሌንጅ ፈንድ፣ የኮፐንሀገን፣ ሳውዝአምፕተን እና የኮርኔል ዩኒቨርሲዎቲች ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋለውን ድህነት ለመቀነስ ለሚከናወኑ ሥራዎችን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተለይም በድህነት ቅነሳ ላይ ለሚሰሩ የምርምር ድርጅቶች እና ተመራማሪዎች ግለሰቦች የገንዘብ እና ሌሎች ድጋፎችን እንደሚያቀርብ ነው የተጠቆመው፡፡

ይህም ተመራማሪዎቹ በኢትዮጵያ ድህነትን ለመቀነስ ለሚከናወኑ ሥራዎች በማስረጃ እና መረጃ ላይ የተመሰረተና ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆን ጥናት እንዲያቀርቡ ያስችላል ተብሏል፡፡

በኦክስፎርድ ፖሊሲ ማኔጅመንት ሚመራው ፕሮጀክቱ ከዓለም ባንክ እንዲሁም ኮፐንሀገን፣ ሳውዝአምፕተን እና ኮርኔል ዩኒቨርሲዎቲዎችጋር በትብብር እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡

“ዲፕ ቻሌንጅ ፈንድ” ፕሮጀክት በኢትዮጵያ በድህነት ቅነሳ ላይ የሚሰሩ ተቋማት ለሚተገብሯቸው ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎች እና ፕሮግራሞች ጠቃሚ ግብዓት እንደሚያስገኝም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.