በሲዳማ ክልል በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና ደራሽ ውኃ የሟቾች ቁጥር 11 ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ እና ደራሽ ውኃ የሟቾች ቁጥር 11 መድረሱን የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በወንሾ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር ዘጠኝ መድረሱን እና ሥድስት ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በይርጋለም ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ መሆኑን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አበራ ዊላ ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም በቡራ ወረዳ በደራሽ ውኃ የሁለት ሕጻናት ሕይወት ማለፉን ለፋና ብርድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጠዋል፡፡
ሕብረተሰቡ የክረምቱን ሁኔታ በመረዳት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግም አሳስበዋል፡፡
በብርሃኑ በጋሻው