Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ ሃዘን ቀን ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የታወጀው ብሔራዊ የሃዘን ቀን ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተከሂዷል፡፡

በወረዳው የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ሕይወታቸው ላለፉ ዜጎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሃዘን ቀን ማወጁ ይታወሳል።

3ኛ ቀኑን ለያዘው ብሔራዊ የሃዘን ቀን ማጠቃለያም በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ውድ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የሃዘን መግለጫ ጧፍ የማብራት መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

በመርሐ-ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የአካበቢው ነዋሪዎች መሳተፋቸውን የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.