የቦሌ መንገድ የመዲናችን አዲስ አበባ የደመቀ የንግድ እና የዘመናዊ እንቅስቃሴ አገልግሎቶች ማዕከል ነው።
ወደቦሌ አለምአቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ እና ወደሌሎች የከተማዋ ክፍሎች ለሚደረግ ጉዞ ለተቀላጠፈ የትራንስፖርት ግልጋሎት የሚውል መስመርም ነው።
በመንገዱ የሚገኙ የተለያዩ የቢዝነስ ማዕከላት፣ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች እና ሱቆች የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኝዎችን ቀልብ የሚስቡ ናቸው።
ለበለፉት ጥቂት ወራት የቦሌ መንገድ በኮሪደር ልማት እንቅስቃሴ የአዲስ አበባን የኢኮኖሚ እድገት እና የከተማ ልማት ጥራት በሚያሳይ ሁኔታ ከፍ ያለ ሥራ ሲሠራ ቆይቷል።
ከቦሌ ድልድይ እስከ መስቀል አደባባይ የተሠራው ሥራ ሌሎች ተግባራትን ጨምሮ የሚከተሉትን ዐበይት ክንውኖች ያካተተ ነው፤
* የ4.3 ኪሎ ሜትር የመንገድ ልማት
* የ10 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ ግንባታ
* የ13.2 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ ግንባታ
* የ30,160 ካሬ ሜትር የግራናይት እና ባሳልት ንጥፍ ሥራ
* የ30 የአውቶቡስ እና ታክሲ መቆሚያ ሥራ
* የ10 የመኪና ፓርኪንግ ስፍራዎች ሥራ
* ከ10 በላይ የሆኑ አነስተኛ የሕዝብ ፓርኮች እና ማረፊያ ፕላዛዎች
* ከ500 በላይ የሚሆኑ የመንገድ ዳር ሕንፃዎች እና ቤቶች ጥገና እና እድሳት
ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት