Fana: At a Speed of Life!

ጀኔራል ሰዓረ መኮንን የተሰዉበት አንደኛ አመት መታሰቢያ ሲከበር በስማቸው የተሰየመው ጎዳናም ተመርቋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀድሞ የኢፌድሪ ኤታማጆር ሹም ጀኔራል ሰዓረ መኮንን የተሰዉበት አንደኛ አመት መታሰቢያ መርሀግብር ተከናወነ።
 
በመርሀግብሩ ላይ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ እና የአዲስአበባ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ተገኝተዋል።
 
ጀኔራል ሰዓረ ባለፈው አመት ህይወታቸው ከማለፉ ከሰዓታት በፊት ከኢንጅነር ታከለ ኡማ ጋር በመሆን ከሩዋንዳ ወደ አትላስ በሚወስደው መንገድ ላይ ችግኝ በጋራ ተክለዋል።
 
የመታሰቢያ መርሀግብሩም በዚህ ስፍራ ተከናውኗል።
 
የከተማ አስተዳደሩ ጀኔራል ሰዓረ ህይወታቸው ሲያልፍ ቦታው ላይ ፓርክ ለማሰራት ይፋ ባደረገው መሰረት የመታሰቢያ ፓርክ ግንባታው በይፋ ተጀምሯል።
 
ከሩዋንዳ ወደ አትላስ በሚወስደው መንገድ ላይም የጀኔራል ሰዓረ መታሰቢያ ሀውልት እንዲቆም ተጠቁሟል።
 
በመታሰቢያ መርሀግብሩ ላይ የጀኔራል ሰዓረ ቤተሰቦችና ወዳጆች እንዲሁም የተለያዩ አመራሮች ተገኝተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.