Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የሚበረታታ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ የሆነውን የአየር ንብረት መዛባት ለመከላከል በሚከናወነው ተግባር ውስጥ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ሥራ የሚበረታታ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በአየር ንብርት ለውጥ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የታዳጊ ሀገራት የባለሙያዎች ቡድን 46ኛ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባዔው ላይም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የሚበረታታ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ ላይ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እና የታዳጊ ሀገራት የባለሙያዎች ቡድን አባላት ተገኝተዋል።
በሰለሞን ይታየው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.