Fana: At a Speed of Life!

በኦሞ ወንዝ ሙላት የተጎዱ ወገኖችን የማቋቋም ሥራ እየተሠራ ነው – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በኦሞ ወንዝ ሙላት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች የማቋቋም ሥራ እየተሠራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በወረዳው የኦሞ ወንዝ ሙላት ያስከተለውን አደጋና የደቀነውን ስጋት ተመልክተዋል።

አቶ ጥላሁን በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ አደጋው ከደረሰ ጊዜ ጀምሮ የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር እና ለዚሁ ዓላማ የተቋቋመ ቡድን ወደ ስፍራው በመላክ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ለመካለከል ጥረት ተደርጓል፡፡

በወንዙ ሙላት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችንም በጀልባ ጭምር በመታገዝ ሕብረተሰቡን የመታደግ እና ወደ ጊዜያዊ መጠለያ በማስፈር ሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ማሽኖችን በመጠቀም ጊዜያዊ የውኃ መፋሰሻ እና የተፋሰስ ልማት ሥራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

በየዓመቱ የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ ለመቀነስ ብሎም ውኃው በሰወች ላይ ጉዳት ሳያደርስ መጠቀም የሚቻልበትን መንገድ በጥናት መለየት እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

በቀጣይም በረጅም ጊዜ ዕቅድ በወንዙ አቅራቢያ በሚገኙ ቀበሌዎች የሚኖሩ ወገኖችን ወደ ሌላ ቦታ የማስፈርና አስፈላጊውን መሰረተ-ልማት የሟሟላት ሥራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.