Fana: At a Speed of Life!

በግለሰብ ቤት በርካታ የኢትዮ ቴሌኮምና የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመድ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በርካታ የኢትዮ ቴሌኮምና የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመድ መያዙን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የካራ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ባደረገው ፍተሻ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ የተከማቹ በርካታ የኢትዮ ቴሌኮምና የኤሌክትሪክ ገመድ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ፖል ላይ የሚታሰር የገመድ ማቀፊያ ይዟል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የምርመራ ሥራ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.