ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ አመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ አመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ መርሐ ግብር በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሄደ።
በመርሐ ግብሩ ከጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ተገኝተዋል፡፡
እንዲሁም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ፣የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የክልል ርእሳነ መስተዳደሮች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ፣ የፓርቲውና የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ አመት የምስረታ በዓል “የሀሳብ ልእልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር መቆየቱ ይታወሳል።
በዓሉም በፓናል ውይይት፣የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ፣ በደም ልገሳ፣ በማስ እስፖርት፣ በፎቶ አውደርዕይ ፣በከተማ ጽዳትና በመሳሰሉ ተግባራት ሲከበር ቆይቷል።