ቼክ ሪፐብሊክ ከአብርኾት ቤተ-መጻሕፍት ጋር እንደምትሠራ አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቼክ ሩፐብሊክ አዲስ አበባ ከሚገኘው አብርኾት ቤተ-መጻሕፍት ጋር ቀጣይነት ያላቸው ሥራዎችን በትብብር ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋገጠች፡፡
የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያን ጁሬስካ አብርኾት ቤተ-መጻሕፍትን ጎብኝተዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም የቤተ-መጻሕፍቱ ዳይሬክተር ውብአየሁ ማሞ (ኢ/ር) ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
ከቤተ-መጻሕፈቱ በተጨማሪም በተቋሙ ሥር ያሉ እንደ ሮቦቲክስ የመሳሰሉ ስልጠናዎች የሚሰጡባቸውን ስፍራዎች መጎብኘታቸው ተገልጿል፡፡
በዚሁ ወቅትም ማሪያን ጁሬስካ ባዩት ነገር መደነቃቸውን ገልጸው÷ ለተቋሙ መጽሐፍትን በሥጦታ አበርክተዋል፡፡
ከተቋሙ ጋርም ቀጣይነት ያላቸውን ሥራዎች ለመስራት ማረጋገጣቸውን የቤተ-መጻሕፍቱ መረጃ አመላክቷል፡፡