ከ9 ሺህ በላይ ሕገ-ወጥ የሽጉጥ ጥይት ተያዘ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሰሜን ወሎ ዞን አንጎት ወረዳ ከ9 ሺህ በላይ ሕገ-ወጥ የሽጉጥ ጥይት ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ለጥፋት አላማ ሊውል የነበረው ጥይቱ መነሻውን ጎንደር ከተማ አድርጎ ወደ ወልድያ-ደሴ ሲጓዝ በነበረ ሚኒባስ ላይ በተደረገ ፍተሻ መያዙ ተገልጿል፡፡
መሰል ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልም ሕብረተሰቡ ለጸጥታ አካላት የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያጠናክር ጥሪ ቀርቧል፡፡