Fana: At a Speed of Life!

አደገኛ ዕፅ በማዘዋወር የተጠረጠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አደገኛ ዕፅ በማዘዋወር የተጠረጠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ኢትዮጵያን የአደገኛ ዕፅ ዝውውር መዳረሻ ለማድረግ በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በአዲስ አበባ ቤት ተከራይተው አደገኛ ዕፅ ሲያዘዋውሩ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ተጠርጣሪዎቹም ችነዱ ቫሊንታነም ችኩማ (ናይጄሪያዊ)፣ ሮባ ይ ዋሲሎ ዜግነት (ኬኒያዊት) እና ጀስቲኒ ላውራንት ኦንጉዌኔ (ካሜሮናዊ ) ናቸው፡፡

አደገኛ ዕፅ በማዘዋወር የተጠረጠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.