Fana: At a Speed of Life!

የመስኖ ልማት የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመከላከል የጎላ ሚና እንዳለው ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስኖ ልማት የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባሻገር የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመከላከል የጎላ ሚና እንዳለው የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አማካሪ ታየ ሙሉጌታ ኢትዮጵያ ያላትን ውሃዎች በመስኖ ተጠቅማ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል፡፡

በዚሁም ያላትን የውሃ ሀብት እና ሰፊ መሬት ተጠቅማ በመስኖ የምትለማ ሀገር መሆኗን አረጋግጣለችም ነው ያሉት።

ከጊዜ ወደ ጊዜ በመስኖ ልማት ከፍተኛ ወጤት እየተመዘገበ መምጣቱን ገልጸው፤ የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖማ ለማሳደግ እንደሚረዳም አንስተዋል፡፡

በአመለወርቅ መኳንንት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.