ሕዳሴ ግድብን መጎብኘት ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ቦታው ድረስ ሄዶ መመልከት ልብን በሐሴት ይሞላል።
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት የስራ ኃላፊዎች የሕዳሴ ግድቡን እና የንጋት ሐይቅን ጎብኝተዋል።
የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ተስፋዬ ዘውዴ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ ኢትዮጵውያን በተባበረ ክንድ ዕውን ያደረጉትን የሕዳሴ ግድብ መጎብኘት ልዩ ስሜት ይፈጥራል።
ግድቡ እውን እንዲሆን ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ማበርከታቸውን አስታውሰው፤ በተለያየ መልኩ ያደረግነው አስተዋጾ ፍሬ አፍርቶ መመልከታችን ደስተኞች አድርጎናል ነው ያሉት።
በጉብኝቱ የተሳተፉ የተቋሙ አመራሮች ግድቡን ዕውን ሆኖ ለሀገር የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ ብሎም ለቀጣይ ትውልድ የሚቀጥል አሻራ መመልከታችን እንደ ልዩ ዕድል የምንቆጥረው ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ታላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት የሆነው ግድቡ በዓባይ ወንዝ ላይ የነበረንን ቁጭት በውጤት አጅቦ የተካ ወደ አንድ ከፍታ ያሸጋገረ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑን መመልከት መቻሉን ገልጸዋል።
ሀገር በርካታ ጫናዎችን በመቋቋም እውን ያደረገችው ግድቡ የልፋት ውጤትን የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በግለሰብም ሆነ በተቋማት ደረጃ ግዙፉን ግድብ እና ንጋት ሐይቅን ሊጎበኙ እንደሚገባ አመልክተዋል።
በግድቡ የፈጠረው የንጋት ሐይቅ፣ ደሴቶች፣ የዓሣ ሃብት እና የቱሪዝም አቅም ለሀገር ከፍታ ትልቅ አስተዋጽዖ ያበረክታል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ፕሮጀክቱ የሀገር የመቻል አቅም የታየበት የዘመናችን ቅርስ ነው ብለዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!