Fana: At a Speed of Life!

በወገራ ወረዳ ነፍጥ አንስተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግሥትን የሠላም ጥሪ ተቀበሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ ነፍጥ አንስተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 48 ታጣቂዎች የመንግሥትን የሠላም ጥሪ ተቀበሉ፡፡

የሠላምን ጥሪ የተቀበሉት አካላት በሰጡት አስተያየት፤ ያሳለፍነው የእርስበርስ ጦርነት ተገቢ እንዳልሆነና ችግሮቻችንን ለመፍታት ውይይት ዋነኛ አማራጭ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል።

በቀጣይም ለሰላም ግንባታ ሥራ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ ነን ማለታቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ አመላክቷል፡፡

የተፈጠረላቸውን ግንዛቤ በመጠቀምም፤ የተሳሳቱትን ወደ ሰላም እንዲመጡ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.