በመጋቢት የደም ልገሣ የንቅናቄ ሥራ እንደሚከናወን ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መጋቢትን የደም ልገሣ ወር በማድረግ የንቅናቄ ሥራዎችን እንደሚያከናውን የኢትዮጵያ ደምና ኅብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታወቀ።
አገልግሎቱ ከበጎ ፈቃደኞች ደምና ኅብረ-ህዋስ በማሠባሠብና ደኅንነቱን በማረጋገጥ ለተጠቃሚዎች እያሥተላለፈ መሆኑን ገልጿል፡፡
አሁን ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን እና የእስልምና ሐይማኖት ተከታዮች የጾም ወቅት መሆኑን ተከትሎ የደምና የደም ተዋፅኦ አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም የተጠናከሩ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ አንስቷል፡፡
በዚህም መጋቢትን የደም ልገሣ ወር በማድረግ አስፈላጊውን ግብዓት ለማሠባሠብ የሚያሥችል ሥራ ለማከናወን ዝግጅት መደረጉን የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡
ለዚህ ሰብዓዊ አገልግሎት፤ በጎ ፈቃደኞች እና ማሕበረሠቡ በንቃት ተሣታፊ እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል።
በሰለሞን ይታየው