Fana: At a Speed of Life!

በከሚሴ ከተማ የሰላምና የልማት ምክክር መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር እና የሰሜን ሸዋ ዞኖች አጎራባች ወረዳዎች ተወካዮች በተገኙበት በከሚሴ ከተማ የሰላምና የልማት ምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

ውይይቱ የተካሄደው፤ “ከረመዳን አስከ ረመዳን፣ ከትንሳኤ እስከ ትንሳኤ” በሚል መሪ ሐሳብ ነው፡፡

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ አሊ በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ ከእስትንፋስ እኩል ዋጋ ላላት ሰላም ሁሉም የበኩሉን ሊያበረክት ይገባል።

እየተሠሩ ባሉ ተከታታይ የልማት ሥራዎች እምርታዊ ለውጦች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ ሰላምን ዘላቂ በማድረግ ረገድ የመድረኩ ሚና የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኤሊያስ አበበ የውይይቱ መነሻ ሠነድ ማቅረባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በመድረኩ ላይ፤ የሁለቱም ዞኖች እና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተሳትፈዋል፡፡

በቀጣይ ሰላምን ለማጽናት በሚከናወነው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም የመድረኩ ተሳታፊዎች አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.