የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴን የሚገመግም መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሀገራዊ የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴን የሚገመግም የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡
ሚኒስትሮችን ጨምሮ በሎጂስቲክስ ዘርፍ የተሰማሩ የዘርፉ አገልግሎት ሰጪዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነው መድረኩ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በዚሁ ወቅት፤ ሚኒስቴሩ የኢትዮጵያን የሎጂስቲክስ ዘርፍ ለማዘመን ብሎም ለማሳደግ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ቀርጾ በመተግበር በዘርፉ አበረታች ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
ሀገራዊ የሎጂስቲክስ ግብን ለማሳካት በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ ያለውን ቅንጅታዊ አሠራር ለማጠናከር እየተሠራ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
በሎጂስቲክስ ዘርፍ የተሰማሩ የዘርፉ አገልግሎት ሰጪዎች፤ የተቋሞቻቸውን የሎጂስቲክስ አገልግሎት አሰጣጥና አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ በሎጂስቲክስ ዘርፍ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ላይ ውይይት በማድረግ የመፍትሔ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ እና የጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተሮች እርስ በርስ የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡
በየሻምበል ምህረት