የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለፕሬዚዳንት ታዬ ዕውቅና ሰጠ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቀድሞ ቦርድ አባሉ ለነበሩት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሽኝት መርሐ-ግብር አካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው በመርሐ-ግብሩ ላይ፤ አየር መንገዱ አኅጉራዊ መሪነቱን እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነቱን እንዲቀጥል ፕሬዚዳንት ታዬ በቦርዱ በነበራቸው ቆይታ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመሥግነዋል፡፡
በተጨማሪም አየር መንገዱ የጥንካሬ የዕድገት እና የአዳዲስ ዕመርታዎች ተምሳሌት ሆኖ እንዲዘልቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው፤ ለተሰጣቸው ዕውቅና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድን ጨምሮ ዋናሥራ አስፈጻሚ እና የማኔጅመንት አባላትን አመሥግነዋል፡፡
አየር መንገዱ በኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነትም በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ የአየር መንገዱ ቦርድ አባል የነበሩት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ ያስሚን ወሀብረቢ ሽኝት ተደርጎላቸዋል።